ቅድመ ማስለቀቅ፣ በማስለቀቅ ወቅት እንዲሁም ድኅረ ማስለቀቅ ጊዜ መንግሥት ሊያሟላ የሚገባቸው የሰብአዊ መብቶች መርሆችን ያልተከተለ ሲሆን በኃይል ማፈናቀል እንደተፈጸመ ይቆጠራል፡፡ ይዞታ የማስለቀቅ ተግባር በአጠቃላይ ሰዎችን ቤት አልባ እንዲሆኑ እና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጋላጭ ማድረግ የለበትም