በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሰመራና አጋቲና ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙ ሰዎች በአፋጣኝና ያለቅድመ ሁኔታ ሊለቀቁ ይገባል። በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ ሕገ ወጥ እና የዘፈቀደ እስር በመሆኑ በአፋጣኝ ሊለቀቁ ይገባል፤ ወደ መኖሪያ አካባቢያቸውም እስኪመለሱ ድረስ በካምፑ ውስጥ ለመቆየት የሚፈልጉ ሰዎች ቢኖሩ በሙሉ ፈቃደኝነትና ያለ ማናቸውም ዓይነት የእንቅስቃሴ ገደብ ሊሆን ይገባል።