መድሏዊ አሠራርን በማስወገድ አካታች የሥራ ቦታን መፍጠር የአካል ጉዳተኞችን የመሥራት መብት ለማክበርና ለማስከበር ያለው አስተዋጽዖ የጎላ ነው
ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ እና የሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ ለማዳበር ሰፊ ተደራሽነት ያለውን የፊልም ጥበብን በመጠቀም በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ ፊልሞች ለእይታ እና ለውይይት ይቀርባሉ
The festival takes place in Adama, Addis Ababa, Bahir Dar, Hawassa & Jigjiga
በሰላም እና ጸጥታ ዘርፍ፣ በፖሊስ፣ በዓቃቤ ሕግ፣ በፍርድ ቤት እና በማረሚያ ቤቶች የሚከናወኑ ሥራዎች በዋነኝነት የሰብአዊ መብቶችን እውን የሚያደርጉ በመሆናቸው አሠራሮቻቸውን ማሻሻል ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መጠበቅ እና መሟላት መሰረት ነው
በክልሉ በሲቪል ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ፣ አካል ጉዳት እና መፈናቀል መጠነ ሰፊ ምርመራን ጨምሮ እየደረሰ ካለው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ጋር የሚመጣጠን የፌዴራል መንግሥቱን አፋጣኝ እርምጃ እና ተጨባጭ ዘላቂ መፍትሔ የሚሻ ነው
በአዳማ፣ አ.አ.፣ ባሕር ዳር፣ ሃዋሳ ወይም ጅግጅጋ ይጠብቁን
ሁለተኛ የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በቅርብ ቀን በአዳማ፣ አ.አ.፣ ባሕርዳር፣ ሃዋሳና ጅግጅጋ ከተሞች ይካሄዳል
በየዓመቱ ከኅዳር 16 - ታኅሣሥ 1 የሚታሰበው የ16ቱ ቀናት የፀረ ጾታዊ ጥቃት ዘመቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ ሲሆን በኢትዮጵያም በብዙ ባለድርሻ አካላት በልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባን ጨምሮ በአምስት ከተሞች የሚካሄደውን ሁለተኛውን የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ነው
የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን "አካታች የፈጠራ ሥራና ሽግግራዊ መፍትሔ ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተደራሽነት" በሚል መሪ ቃል ይታወሳል