መንግሥት በጉዳዩ ዙሪያ የተፈጠረውን አለመተማመን አምኖ የበለጠ ግልጽ እና አሳታፊ ውይይት እንዲያደርግ ኢሰመኮ ጠይቋል
የክልል ልዩ ኃይሎችን “መልሶ ለማደራጀት” በመንግስት የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በአማራ ክልል በተካሄዱ ተቃውሞዎች ላይ በተወሰዱ “እርምጃዎች እና ጥቃቶች”፤ የሰዎች ሞት እና የአካል ጉዳት መከሰቱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
ኢሰመኮ ከመደበኛው የክትትል እና ምርመራ ሥራው ጎን ለጎን ምክረ ሐሳቦችን በመስጠት የተፈጠረው ችግር በውይይት እንዲፈታ ጥረት እያደረገ ይገኛል
መንግሥት የሀገሪቱ ዐቅም በፈቀደ መጠን አስፈላጊ እርምጃዎችን በመመውሰድ የሕፃናት በቂ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብትን ለማረጋገጥ ቀዳሚ ባለግዴታ ነው
የብሔራዊ ምርመራ/ግልጽ ምርመራ በሕዝብ ፊት የሚካሄዱ የአቤቱታ መቀበያ መድረኮቹን ተከትሎ ግኝቶችን እና ምክረ ሐሳቦችን የያዘ ሪፖርት ይፋ የሚደረግ ይሆናል
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ ኢትዮጵያን በሚመለከት በቅርቡ ያወጣው የሰብአዊ መብት ሪፖርት፣ ከጣምራ ቡድኑ ሪፖርት ጋራ በአመዛኙ ተመሳሳይ እንደ ኾነ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ገለጹ
በኮሚሽኑ የሴቶችና ህጻናት መብቶች ኮሚሽነር መስከረም ገስጥ በመግለጫው እንዳሉት ከህግ አግባብ ውጭ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ በማተኮር አቤቱታዎች የሚደመጡ ይሆናል
ነጻነታቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ እና በዘፈቀደ ተነፍገናል የሚሉ ሰዎችን አቤቱታ መቀበያ መድረክ በባሕርዳር ከተማ ሊያካሂድ መኾኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገልጿል
ስምምነቱ “የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው የሲቪክ ማኅበራትን ጨምሮ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት በሕዝባዊ ምክክር የሚገኙ ግብአቶችን መሠረት አድርጎ እና መደበኛ ሀገራዊ የፖሊሲ አወጣጥ ሂደቶችን ተከትሎ ሊዘጋጅ እንደሚገባ” ያስቀምጣል
«ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ባደረሱበት ከተማ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ ተፈናቃዮችን ቤትለቤት እየዞሩ በተለይ የአማራ ብሔር ተወላጆችን ለይተው ገድለዋል» በማለት የምርመራ ግኝቱ ጠቁሟል