የግልጽ የምርመራ መድረኩ ተጎጂዎች፣ ባለግዴታዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እልባት ለማስገኘት እና አስቀድሞ ለመከላከል የመፍትሔ ሐሳቦችን ያመላከተ ነው
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ መሠረት "ከቤቶቹ ባለቤቶች ጋር በክፍለ ከተማ፣ በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ውይይት ተደርጎ በቂ ግንዛቤ" እንዲፈጠር መደረጉን ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል
በኦሮሚያ ክልል፣ ዐዲስ በመመሥረት ላይ በሚገኘው በሸገር ከተማ በተፈጸመው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ የማንሣት ርምጃ የተጎዱ ሰዎች፣ በሕጋዊ መንገድ የመኖሪያ ቤት ሊያገኙ እንደሚገባ ኢሰመኮ አሳሰበ
ሚሊዮን ዜጎቿ ተፈናቅለው የችግርና የሰቀቀን ኑሮ እየገፉ ቢሆንም የእነሱን ጉዳይ ጉዳዬ ብሎ የሚሰራ ተቋም የትኛው ነው ብላችሁ ብትፈልጉ አታገኙም
ከሰብአዊ መብቶች አኳያ ሊቀጥሉ እና ሊበረታቱ የሚገባቸው መልካም አሠራሮች ቢኖሩም የአረጋውያን መንከባከቢያ ማእከላቱ በአብዛኛው ቋሚ የገቢ ምንጭ የሌላቸው እና በገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ ያላቸው ተሳትፎም ውስን መሆኑ አገልግሎታቸውን ለማስቀጠልና ዘላቂነቱን (sustainability) ለማረጋገጥ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል
የመሬት መብት ከምግብ፣ ከጤና፣ ከመጠለያ፣ ከውሃ፣ ከባህላዊ መብቶች ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው በመሆኑ መሬት ነክ ድንጋጌዎችና ፖሊሲዎች ሰብአዊ መብቶች መር ሊሆኑ ይገባል
«ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ባደረሱበት ከተማ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ ተፈናቃዮችን ቤትለቤት እየዞሩ በተለይ የአማራ ብሔር ተወላጆችን ለይተው ገድለዋል» በማለት የምርመራ ግኝቱ ጠቁሟል
ኮሚሽኑ ያወጣው የምርመራ ዘገባ እንደሚያሳየው ከተገደሉት ሰዎች መካከል 42ቱ በተፈናቃዮች የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እና ከተቀባይ ማኅበረሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ ተፈናቃዮች እንዲሁም መንግሥትን ይደግፋሉ የተባሉ ነዋሪዎች ነበሩ
የመንግሥት የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር አካላት በሙሉ በበቂ ምክንያት በወንጀል የተጠረጠረን ሰው በተለይም በቅድመ ምርመራ ወቅት የዋስትና መብት አጠባበቅ ሥርዓትን ባከበረ መንገድ ምርመራ ከማድረግ ውጪ ተገቢ ያልሆነ እስርን ማስወገድ አለባቸው
መንግሥት የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት ከማስጠበቅ በተጨማሪ ለግጭቱ ዘላቂ እና ሰላማዊ መፍትሔ ለማበጀት ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ አለበት