Everyone shall have the right to freedom of expression in the form of art
ማንኛውም ሰው በሥነ-ጥበብ መልክ ሐሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብት አለው
የታራሚዎችን የተሻለ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ለማረጋገጥ በባለድርሻዎች የሚደረገው ድጋፍ በትብብር መርሕ ሊቀጥል ይገባል
In all actions concerning children, whether undertaken by public or private social welfare institutions, courts of law, administrative authorities or legislative bodies, the best interests of the child shall be a primary consideration
በመንግሥታዊም ሆነ በግል የማኅበራዊ ደኅንነት ተቋማት፣ በፍርድ ቤቶች፣ በአስተዳደር ባለሥልጣኖች ወይም በሕግ አውጪ አካላት በሚወሰዱ ማናቸውም ሕፃናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች የሕፃናት ደኅንነትና ጥቅም በቀዳሚነት መታሰብ አለበት
የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የትምህርት መብት ለማረጋገጥ የመምህራንን ግንዛቤ በማዳበር የትምህርት አሰጣጡ ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ እንዲሆን ማስቻል ይገባል
ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጡ ምትክ ቦታዎች ከባቢያዊ ተደራሽነትን በበቂ ሁኔታ ያሟሉ መሆን አለባቸው
ምግብ የማግኘት መብትን ለማረጋገጥ እና ሰብአዊ መብቶች ተኮር ለማድረግ የመንግሥትን እና የባለድርሻዎችን ጥምር ጥረት ይጠይቃል
አሠሪዎች በቁጥጥራቸው ሥር ያሉ የሥራ ቦታዎች፣ ማሽኖች፣ መሣሪያዎች እና የአሠራር ሂደቶች ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ደኅንነታቸው የተጠበቀ እና ምንም የጤና ሥጋት የማያስከትሉ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ሊደረጉ ይገባል
ሰላምና ደኅንነትን የማስከበር፣ ወንጀል የመከላከልና የመመርመር ሥራ በሕግ አግባብ ብቻ ሊሆን ይገባል