ሰዎች በሰላም ወጥቶ የመግባት፣ ከቦታ ቦታ በነጻነት የመንቀሳቀስ እና የመሥራት መብቶቻቸው እንዲከበሩና መልካም እመርታዎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው የትጥቅ ግጭቶችን ግልጽ እና አካታች በሆነ ሂደት ማስቆም፣ በቁርጠኝነት የሕግ የበላይነትን ማስከበር ይገባል
ስልጠናዎቹ በአካል ጉዳተኞች፣ በሕፃናት፣ እንዲሁም በሕግ ታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው
በሥራ ዘርፉ የሚንቀሳቀሱ አስፈጻሚ ተቋማትን በማጠናከር፣ ባለድርሻዎችን አቀናጅቶ እና አስተባብሮ የሚመራ ሥርዓት መዘርጋት አለበት
ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሁለት መቶ የሚሆኑ ኤርትራዊያን በግዳጅ ወደ ኤርትራ እንዲመለሱ መደረጋቸው እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአብዛኛው በመንግሥት ሲቀርብ በነበረው የጤና አገልግሎት ላይ የግሉ ዘርፍ በሰፊው መሰማራቱ ሊበረታታ እንደሚገባው ገልጸው፣ ተቋማቱ ካላቸው የፋይናንስ ተደራሽነት አንጻር ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ አስታውቀዋል
የጤና መብትን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የግሉ ዘርፍ እና የመንግሥት አካላት ተቀናጅተው ሊሠሩ ይገባል
ሰላማዊ በሆኑ ሃይማኖታዊ ስብስቦች ወቅት የሚወሰድ እርምጃ በተለይም የመንግሥት የጸጥታ አካላትን ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆኑን በድጋሚ እናሳስባለን
ጉብኝቱ የኮሚሽኑ ምክረ ሐሳቦች በአስፈጻሚው እንዲተገበሩ የምክር ቤቱን ተጨማሪ ድጋፍ ለማግኘት የሚረዳ ነው
በሀገር ውስጥ በሰዎች የመነገድ ተግባር በተለይም በሴቶችና ሕፃናት መነገድ ሰፊና ውስብስብ ችግር በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሻል
ኮሚሽኑ በአወጣው መግለጫ፣ በከተማዋ፣ የአደባባይ በዓላት ሲከበሩ እና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች በሚኖሩበት ጊዜ፣ የጎዳና ላይ ሕፃናት ከየቦታው ያለፈቃዳቸው እየተሰበሰቡ በጅምላ ተይዘው ወደ ማቆያ ሥፍራ ይወሰዳሉ፤ ብሏል