የተሻለ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እና በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቅባቸዋል
አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን የተመለከቱ ህጎች እና ተቋማዊ ማዕቀፎች እንዲዘጋጁ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ
አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ከተቋማዊ የአሠራር ክፍተቶችና ከተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳ የሚገጥሟቸውን መሰናክሎች ለመቅረፍ ወጥ ተቋማዊ መዋቅር መዘርጋት እንደሚያስፈልግም ነዉ የገለጸዉ
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ም/ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለውን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት አባል ዶ/ር ካሣ ተሻገርን ጨምሮ 53 ሰዎች አዋሽ አርባ ውስጥ ባለ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ መታሰራቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አረጋገጠ
ኮሚሽኑ ይህን ያለው ዋና ኮሚሽነሩ ዳንዔል በቀለን ጨምሮ አምስት የኮሚሽኑ ባለሙያዎች የሚገኙበት ቡድን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በቁጥጥር ሥር ውለው አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን ታሳሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. መጎብኘቱን አስመልክቶ ዛሬ ነሐሴ 27 ባወጣውና ለአሻም በላከላት መግለጫ ላይ ነው
አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ከተቋማዊ የአሠራር ክፍተቶችና ከተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳ የሚገጥሟቸውን መሰናክሎች ለመቅረፍ ወጥ ተቋማዊ መዋቅር መዘርጋት ያስፈልጋል
Everyone has the right to education. Primary education shall be compulsory and available free to all
ማንኛውም ሰው የመማር መብት አለው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት መማር ግዴታ ሊሆንና ለሁሉም ሰው በነጻ ሊሰጥ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዋሽ አርባ በሚገኘው የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በእሥር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን መጎብኘቱን ትናንት ቅዳሜ ነሐሴ 27 ባወጣው መግለጫ አስታወቀ
አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የሀገር መከላከያ የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን እነዚህን ታሳሪዎች፣ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ 5 የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ትላንት ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. መጎብኘታቸው በመግለጫው ተጠቅሷል