በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የጥቃት ተጎጂ ሴቶችና ሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝን ለማሻሻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር ያስፈልጋል
ይህን ስምምነት የተቀበሉ ሀገራት በገጠር ሴቶች ላይ የሚደረግ አድሎአዊ ልዩነት በማጥፋት ሴቶች ከወንዶች እኩል በገጠር ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሳተፉና ከዚሁም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ተገቢውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ
State parties shall take all appropriate measures to eliminate discrimination against women in rural areas in order to ensure that they participate in and benefit from rural development
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ በአንዳንድ ፖሊስ ጣቢያዎች እድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ተጠርጣሪዎች ለአካለ መጠን ከደረሱ ተጠርጣሪዎች ጋር ተቀላቅለው የሚታሰሩ መሆናቸውን ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ገልጿል
በሀገሪቱ በተከሰቱ ሰው ሠራሽ ቀውሶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች ሳቢያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶችና ሕፃናትን ለመፈናቀል፣ ለጾታዊ ጥቃቶች እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲሁም ለሌሎች ተደራራቢ የመብት ጥሰቶች ተጋላጭነታቸውን እንደጨመረ በሪፖርቱ ገልጿል
በሕግ፣ በፖሊሲና በአሠራር ረገድ የኮሚሽኑን ምክረ ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ ለሴቶች እና ለሕፃናት መብቶች የተሻለ ጥበቃ ማድረግ ይገባል
ይህ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት በተለይ የሴቶችና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ በዝርዝር በማተኮር ኮሚሽኑ የለያቸውን አበረታች እመርታዎችን፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን እና ምክረ-ሐሳቦችን አካቷል