



የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ እና ያደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ከየካቲት 14 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በድርቁ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብለው በተለያዩ አካላት በይፋ እውቅና የተሰጣቸው አካባቢዎች በመዘዋወር የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል በማድረግ ያዘጋጀውን ባለ 40 ገጽ ሪፖርት።



ይህ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ድረስ በተለያዩ የሥራ ክፍሎቹ እና ጽ/ቤቶቹ አማካኝነት ባደረገው ክትትልና ምርመራ፣ ባከናወናቸው መለስተኛ ጥናቶች፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ ባካሄዳቸው ምርመራዎች፣ በውትወታ እና በሌሎች ተግባራቶቹ አማካኝነት ከተገኙ መረጃዎች የተዘጋጀ ነው። ሙሉ ሪፖርቱ...
