ውጤታማ እና ትርጉም ያለው የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎን ለማረጋገጥ የግምገማና የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት ቁልፍ ተግባራት ናቸው
ተማሪዎቹ አገልግሎት በሚያገኙባቸው ቢሮዎች ፣ በትምህርት እና መልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች እና በሌሎች የመብት ጥሰት ይደርስባቸዋል ተብሏል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በአምስቱ ላይ ባደረገው ክትትል፣ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጉዳይ የሚመራበት የጽሑፍ ፖሊሲ እንደሌላቸው ማረጋገጡን አስታወቀ
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከባቢያዊ፣ ተቋማዊ፣የመረጃና ተግባቦት እንዲሁም ከአመለካከት ጋር ከተያያዙ ተግዳሮቶች ነጻ መሆን አለባቸው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በሕግ ከተሰጡት ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል የሰብአዊ መብቶች ክትትል ማድረግ አንዱ በመሆኑ፤ በተለይ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረጉ የክትትል ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ በዚህም መሠረት ኮሚሽኑ የአካል ጉዳተኞች የከፍተኛ ትምህርት ተካታችነትን ሁኔታ ለመፈተሽ ያስችለው ዘንድ የኢትዮጵያ የሕግ እና የፖሊሲ ማዕቀፎች እንዲሁም አጠቃላይ ከባቢያዊ፣ ተቋማዊ፣ የመረጃ እና የአመለካከት ተደራሽነትን...
በባሕርይ እና በማኅበራዊ ለውጥ ዙሪያ የሚሠሩ አካላት ብዝኃነትን ማዕከል በማድረግ የአረጋውያንን እና የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊ መብቶች በማስፋፋት ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው
የንግድ ቤቶችን የማፍረስ ሂደት ሕጋዊ ሥርዓትን መከተልና በተለይ በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ ከግንዛቤ በማስገባት መከናወን አለበት
በተለያዩ አካባቢዎች እየተባባሱ ናቸው ለተባሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈጻሚውን አካል እንዲጠይቅና እንዲያሳስብ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥያቄ አቀረበ
በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ የንፁሃን ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው ተብሏል
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ባቀረቡት ሪፖርት፣ በአማራ ክልል እየተከናወነ ባለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እስካሁን ድረስ በንፁኃን ሰዎች ላይ የሞት፣ የመቁሰል፣ የሀብት ውድመትና የመፈናቀል ጉዳት ከመድረሱም በላይ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን ተናግረዋል