ከሰብአዊ መብቶች አኳያ ሊቀጥሉ እና ሊበረታቱ የሚገባቸው መልካም አሠራሮች ቢኖሩም የአረጋውያን መንከባከቢያ ማእከላቱ በአብዛኛው ቋሚ የገቢ ምንጭ የሌላቸው እና በገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ ያላቸው ተሳትፎም ውስን መሆኑ አገልግሎታቸውን ለማስቀጠልና ዘላቂነቱን (sustainability) ለማረጋገጥ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል
ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ እውነትን ለማውጣት፣ ማኅበረሰባዊ እርቅ እና ፈውስ ለማምጣት እንዲሁም የተጎጂዎችን መፍትሔ የማግኘት መብትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ተግባራዊ መደረግ አለበት
ሰዎች ሁሉ በሕግ ፊት እኩል ናቸው፤ ያለምንም ልዩነት እኩል የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው
Female circumcision and related acts are punishable by Articles 565 and 566 of the FDRE Criminal Code
የሴት ልጅ ግርዛት እና ተያያዥ ድርጊቶች በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ፣ አንቀጽ 565 እና አንቀጽ 566 መሠረት የሚያስቀጡ ተግባራት ናቸው
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በትምህርት ተቋማት የሚያጋጥማቸውን የከባቢያዊ፣ የአመለካከት፣ የተግባቦት እና ተያያዥ ተቋማዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል
በስደተኞች ሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ፤ በመንግሥት እና በተራድኦ ተቋማት ለስደተኞች የሚቀርቡ የሰብአዊ ድጋፍ እና ሌሎች አገልግሎቶች አካታች፣ ተደራሽ እና ሰብአዊ ክብራቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ይረዳል
ኢሰመኮ እንዳስታወቀዉ በየአካባቢዉ ስለሚፈናቀለዉ ሕዝብ በቂ መረጃ ባለመጠናቀሩ ለችግር ለተጋለጠዉ ተፈናቃይ የሰብዓዊ ድጋፎችን ለማቅረብ እንቅፋት ሆኗል
Education shall be provided in a manner that is free from any religious influence, political partisanship or cultural prejudices
ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተጽዕኖዎች ነጻ በሆነ መንገድ መካሄድ አለበት