ማንኛውም ሰው መረጃን የመፈለግ፣ የመቀበል እና የማሰራጨት መብት አለው፡፡(ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 19)
መረጃ የማግኘት መብት ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አካል ነው፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 29
ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው፡፡
ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም አይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል፡፡