ኮሚሽኑ በለቀቀው መግለጫ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ካለው የትጥቅ ችግር ጋር በተያያዘ በአንዳንድ አካባቢዎች የሕግ ማስከበሩ በመላላቱ ሰላማዊ ዜጎች በታጣቂዎች፣ በተደራጁ ቡድኖች እና በአንዳንድ የመንግሥት የፀጥታ አካላት የሚደርስባቸው እገታ ተባብሷል ብሏል
ወንጀሉ በአብዛኛው እንደ ገቢ ማስገኛ የተወሰደ መሆኑን የሚጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ድርጊቱ "በተደጋጋሚ፣ በተንሰራፋና በተደራጀ መልኩ እንደሚፈጸም፤ አልፎ አልፎም እንደ በቀል፣ ለፖለቲካ ዓላማ ወይም የታገተ ሌላ ሰውን ለማስለቀቅ በሚል በአጸፋ መልኩ የሚፈጸም መሆኑን" ስለመረዳቱ አመልክቷል
በኦሞ ወንዝ የላይኛው ተፋሰስ አካባቢዎች ከነሐሴ ወር የመጀመሪያ ቀናት ጀምሮ በጣለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ምክንያት የዳሰነች ወረዳ ዋና ከተማ በሆነው የኦሞራቴ ከተማ እንዲሁም ቻይና ካምፕ በተባሉ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ በውሃ የመጥለቅለቅ ሥጋት ተጋርጦባቸዋል ብሏል
በዚህ ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሲቪልና የፖለቲካ እንዲሁም የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጅብሪል ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት፥ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዉን ተከትሎ ለግል ድርጅት ተቀጣሪ ሰራተኞችም የደሞዝ ማሻሻያ መደረጉ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል
በተለይም ሴት ሕፃናት የመማር መብታቸውን ከማጣታቸው አልፎ ለ ያለ ዕድሜ ጋብቻ እና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲሁም ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸው፣ ወደ ከተማ እየፈለሱና ለጉልበት ብዝበዛ እየተዳረጉ መሆኑን ኮሚሽኑ አመልክቷል
በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ባሉ ግጭቶች እና በሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ ከ5500 በላይ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራቸውን ከማከናወን ውጪ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ
ኢሰመኮ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራባቸው የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች መካከል በፖሊስ ጣቢያዎች እና በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎችን የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን በተመለከተ የመከታተልና ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ ከተቋሙ ባገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል
በተለይም ግጭት ባለባቸው በኦሮሚያ፣ አማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በታጣቂዎች በሚፈጸም ጥቃት እና መንግሥት ያንን ለመከላከል አልያም ለፍትሕ ለማቅረብ በሚደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ንፁሐን እየሞቱ እና እየተጎዱ መሆኑን መንግሥታዊው የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪው ኢሰመኮ ተናግሯል
በ2016 ዓ.ም. በበርካታ የኢትዮጵያ አከባቢዎች በተለምዶ ወቅታዊ ሁኔታ በሚል ምክንያቶች ሳቢያ ሰዎች ለዘፈቀደ እስር እንዲሁም ለአስገድዶ መሰወር የተዳረጉበት በርካታ ክስተቶች መመዝገቡን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
ኮሚሽኑ ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው 3ኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ይፋ አድርጓል