የእርቅ ሂደቱ የወንጀል ተጠያቂነትን መተካት ወይም ማስተጓጎል የለበትም
የሕግ አስከባሪዎች ሕግ ሊያከብሩ ይገባል
ፍትሕ እና የተጎዱ ሰዎችና ቦታዎችን መልሶ መጠገን የሁሉንም ወገኖች ቁርጠኝነት ይፈልጋል
በሕዝብ እና በየደርጃው ያሉ የመንግስት አካላት በአንድ መድረክ ቀርበው በተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ፈጣን ውጤት ለማምጣት ያስችላል
ያቀረባቸው ምክረ ሃሳቦች እንዲፈጸሙ የጣምራ ምርምር ቡድኑ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል
ለሟቾች ቤተሰቦች እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ለደረሰባቸው ጉዳት ተገቢ የሆነ ካሳ ሊሰጣቸው ይገባል
ከጠንካራ የግምገማ ሂደት በኋላ የሚሰጠውን የዓለም አቀፉ የብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋማት ጥምረት (Global Alliance of National Human Rights Institutions (GANHRI)) የደረጃ “A” (አንደኛ ደረጃ) እውቅና ማግኘቱ ኮሚሽኑ የፓሪስ መርሆችን ሙሉ በሙሉ ማሟላቱን የሚያሳይ ነው።
በአጠቃላይ ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል ለማረጋገጥ እንደቻለው ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መተግበር ባለበት መንገድ በተለይም “የጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት እና ከመድልዎ ነፃ መሆን” የሚሉትን የሰብአዊ መብት መርሆዎችን ባከበረ መልኩ አለመተግበሩን ተመልክቷል።
ስልጠናው ወጣቶች በሰላም በጋራ መኖርን እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ካሉ ልዩነቶችን መሰረት አድርገው የሚከሰቱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመከላከል ሥራ ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ የማስቻል አላማ ያለው ነው፡፡
ኢሰመኮ ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ባደረገው ውይይት የታሳሪዎችን ደህንነት ስለማረጋገጥ መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎች ላይ ተመካክሯል