የ2016 ዓ.ም. የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በሕይወት የመኖር መብት እና በቂ የሆነ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ ኅዳር 30 ቀን የሚውለው የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብቶች መግለጫ 75ኛ ዓመት የሚታሰብበት ዝግጅት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፤ ሁሉም ሰው በውድድሩ እንዲሳተፍ እና ሂደቱን እንዲከታተል ተጋብዟል
ማንኛውም አእምሮው ወይም አካሉ የተጎዳ ሕፃን ከመንፈሳዊና ከአካላዊ ፍላጐቱ ጋር የተጣጣመ እንዲሁም ክብሩን የሚያረጋግጥ፣ በራስ መተማመኑንና በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ የሚያሳድግ የተለየ የጥበቃ እርምጃ ተጠቃሚ የመሆን መብት አለው
A child who is mentally or physically disabled shall have the right to special measures of protection in keeping with his physical and moral needs and under conditions which ensure his dignity and promote his self-reliance and active participation in the community
የቁም ነገር መጥሄት ባልደረቦች ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የሄደባቸውን መንገዶች እንዲሁም ያወጣቸውን ተከታታይነት ያላቸውን ሪፖርቶች መርምረው ዶ/ር ዳንኤልንና የሚመሩትን ኮሚሽን በዓመቱ ሃላፊነቱን በአግባቡ የተወጣ የመንግስት መስሪያ ቤት ብለዋቸዋል
አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን የተመለከቱ ህጎች እና ተቋማዊ ማዕቀፎች እንዲዘጋጁ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ
አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ከተቋማዊ የአሠራር ክፍተቶችና ከተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳ የሚገጥሟቸውን መሰናክሎች ለመቅረፍ ወጥ ተቋማዊ መዋቅር መዘርጋት እንደሚያስፈልግም ነዉ የገለጸዉ
አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ከተቋማዊ የአሠራር ክፍተቶችና ከተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳ የሚገጥሟቸውን መሰናክሎች ለመቅረፍ ወጥ ተቋማዊ መዋቅር መዘርጋት ያስፈልጋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀውን የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ሁኔታ የተመለከተ ባለ 44 ገጽ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ዓመታዊ የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት በተለይ በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ላይ በዝርዝር በማተኮር በበጀት ዓመቱ የታዩ መልካም...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራባቸው የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች መካከል የአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች አንዱ ነው። ለዚህም ዘርፉን የተመለከተና በኮሚሽነር የሚመራ የሥራ ክፍል በማቋቋም፤ በአረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች መብቶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስፋፊያ፣ የሕግ ማእቀፎች አተገባበር ክትትልና ምርመራ እንዲሁም ዘርፈ-ብዙ የውትወታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ኮሚሽኑ በሕግ በተሰጡት ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነቶች መሠረት ያከናወናቸውን የሰብአዊ...
ከግጭቶች በኋላ በሚከናወኑ የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች የአካል ጉዳተኞችን እና የአረጋውያንን ትርጉም ያለው ተሳትፎ  ማረጋገጥ ያስፈልጋል