ማንኛውም አካል ጉዳተኛ ሰው ዘርን፣ ጎሳን፣ የቆዳ ቀለምን፣ ጾታን፣ ቋንቋን፣ ሃይማኖትን፣ ፖለቲካን ወይም በሌላ ዐይነት አመለካከት፣ በብሔራዊ ወይም ማኅበራዊ መሠረትን፣ ሃብትን፣ ትውልድን ወይም ሌላ ሁኔታን ጨምሮ በማንኛውም ምክንያት ማንኛውም ዐይነት ልዩነት ሳይደረግበት በዚህ ፕሮቶኮል ውስጥ ዕውቅናና ዋስትና የተሰጣቸው መብቶች እና ነጻነቶችን የማግኘት እና የመጠቀም መብት አለው
Every person with a disability shall be entitled to the enjoyment of the rights and freedoms recognised and guaranteed in this Protocol without distinction of any kind on any ground including, race, ethnic group, colour, sex, language, religion, political or any other opinion, national and social origin, fortune, birth or any status
አባል ሀገራት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ሁሉም ዐይነት ጥቃቶችን የሚከለክሉ ሕጎችን ለማውጣት እና ለማስፈጸም ተገቢ እና ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው
States Parties shall take appropriate and effective measures to enact and enforce laws to prohibit all forms of violence against women
ማንኛውም ሕፃን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፤ በትምህርቱ፣ በጤናውና በደኅንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎችን እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብት አለው
Every child has the right not to be subjected to exploitative practices, neither to be required nor permitted to perform work which may be hazardous or harmful to his or her education, health or wellbeing
ተዋዋይ ሀገራት የማናቸውም ዐይነት የእንክብካቤ እጦት፣ ብዝበዛ፣ ያልተገባ አያያዝ፣ ማሰቃየት ወይም ሌላ ማናቸውም ዐይነት ጭካኔ የተሞላበት፣ ኢ-ሰብአዊ የሆነ ወይም ክብርን የሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት ወይም የትጥቅ ግጭት ሰለባ የሆነን ሕፃን በአካልና በሥነ ልቦና ከደረሰበት ጉዳት እንዲያገግምና ከኅብረተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል ለማድረግ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ
States Parties shall take all appropriate measures to promote physical and psychological recovery and social reintegration of a child victim of any form of neglect, exploitation, or abuse; torture or any other form of cruel, inhuman or degrading treatment or punishment; or armed conflicts