ግድያዎቹ የተፈጸሙት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም በክልሎቹ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች እንደሆነ ኢሰመኮ ዓርብ፣ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም. ያወጣው ሪፖርት አመልክቷል
Commission calls for immediate release of detainees held incommunicado
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በግጭት ዐውድ ውስጥ ያሉ አካባቢዎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በአሳሳቢ ሁኔታ መቀጠላቸው በሪፖርቱ ገልጿል
ኮሚሽኑ እንደለጸው ሪፖርቱ ከመስከረም ወር አጋማሽ 2017 ዓ.ም. እስከ ታኅሣሥ 2017 ዓ.ም. አጋማሽ ባለው ጊዜ ውስጥ ያለውን ጊዜ የሚመለከት ነው ብሏል፡፡ ሪፖርቱ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በሙሉ የሚሸፍን አይደለም ያለው ኮሚሽኑ በእነዚህ አካባቢዎች በነጻነት ተንቀሳቅሶ የተሟላ ክትትልና ምርመራ ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ፣ ውጤታማ ክትትልና ምርመራ የተከናወነባቸውን ጉዳዮች ብቻ በማሳያነት እንዳቀረበም ገልጿል
የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታ፣ በመዘዋወር መብትና በመጓጓዣ መንገዶች ላይ የሚፈጸም ሕገ-ወጥ ገደብ፣ የሀገር ውስጥ መፈናቀል እና የዳኝነት ነጻነት መሸርሸሮች እንዳሉም ኢሰመኮ በሪፖርቱ ላይ ጠቅሷል
ይህ የሩብ ዓመት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በተለይ በግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ ከፍተኛ በሆኑ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና አሳሳቢነታቸው በቀጠሉ ጉዳዮች ላይ አጠቃላይ ምልከታ በመስጠት ለሰብአዊ መብቶች ሁኔታ መሻሻል ምክረ-ሐሳቦችን የሚያቀርብ ነው
ስልጠናዎቹ ለፖሊስ፣ ለማረሚያ ቤት አባላት፣ ለወጣቶች፣ ለሴቶች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሙያዎችና የሥራ ኃላፊዎች የተሰጡ ናቸው
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደቀድሞ ቀያቸው የመመለስ እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ የማድረግ ሂደት ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል
Everyone has the right to education. Education shall be free, at least in the elementary and fundamental stages. Elementary education shall be compulsory
ማንኛውም ሰው የመማር መብት አለው፡፡ ቢያንስ የአንደኛ ደረጃና መሠረታዊ ትምህርት በነጻ ሊሰጥ ይገባል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ግዴታ ሊሆን ይገባል