States Parties shall prohibit through legislative measures backed by sanctions, all forms of female genital mutilation (FGM)
አባል ሀገራት ቅጣትን የሚያስከትሉ ሕጎችን በማውጣት ማንኛውንም ዐይነት የሴት ልጅ ግርዛትን መከልከል አለባቸው
የሰብአዊ መብቶች ሥራ የኢሰመኮ ሠራተኞችን እና የሁሉም ባለድርሻ አካላትን ትብብርና ቅንጅታዊ ሥራን ይጠይቃል
ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ ይባላሉ። በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ናቸው
While wishing the new Chief Commissioner a successful term, Deputy Chief Commissioner reiterated the importance of human rights work
የመልካም ሥራ ዘመን መልእክታቸውን ባስተላለፉበት ወቅት ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የሰብአዊ መብቶችን ሥራ አስፈላጊነት አስታውሰዋል
ከአደባባይ በዓላትና ከዓለም አቀፋዊና አኅጉራዊ ስብሰባዎች ጋር በተያያዘ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎችን በግዳጅ ወደ ማቆያ ማዕከል ማስገባትና ማቆየት ሊቆም ይገባል ሲል፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ
በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ “ቃሊቲ አካባቢ” ተብሎ በሚጠራው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ባለ 'ሰፊ መጋዘን' ውስጥ፤ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውንና ይህ ሰዎችን የመያዝና ወደ ማቆያ ማዕከል የማስገባት ድርጊት አሁንም መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል
ከጎዳና ላይ ለሚነሱና ወደማቆያ ለሚገቡ ሰዎች ሰብአዊ መብቶችን ያማከለ ዘላቂ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል
በኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) መሠረት የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ዕጩዎች ጥቆማ እስከ ታኅሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚቆይ ነው