በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በሰዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እና መፈናቀል እልባት ለመስጠት የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል መንግሥታት በዞኑ በቂ የጸጥታ አካላትን ማሰማራትና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ጨምሮ አፋጣኝ፣ ተጨባጭና ዘላቂ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል
ኢሰመኮ እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እና የሰላም ግንባታን በተመለከተ በጋራ ለመሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት (“የጅማ ስምምነት”) ተፈራርመዋል
የተጎጂዎች ማኅበራትን ተሰሚነትና ደህንነት ማጠናከር በሽግግር ፍትሕ ሂደት ለሚኖራቸው ትርጉም ያለው ተሳትፎ ጉልህ ሚና ይጫወታል
ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2019 ዓ.ም. የምታዘጋጀው የአፍሪካ ብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋማት ትስስር (NANHRI) ጠቅላላ ጉባኤ እና በየሁለት ዓመቱ የሚያካሂደውን 16ኛው ኮንፈረንስ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ባለድርሻዎች ቀና ትብብር እና እገዛ እንዲያደርጉ፣ ኢሰመኮ የሚሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበሩ ኢሰመኮ ጥሪ ያቀርባል
በወንጀል ነክ ነገር ውስጥ ገብተው የተገኙ ሕፃናት ማቆያ እና ተሐድሶ ማእከላት ባለሙያዎች የሕፃናቱን ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ለማሻሻል እና ለሕፃናቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ጉልህ ሚና አላቸው
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ እና የጋና የሰብአዊ መብቶችና የአስተዳደር ፍትሕ ኮሚሽን (CHRAJ) ከፍተኛ አመራሮች ተቋማዊ ትብብርን ለማጠናከር እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችል ውይይት አካሂደዋል
ኢሰመኮ ከአፍሪካ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ትስስር እና ከአባል ተቋማቱ ጋር በመተባበር 16ኛውን ዓመታዊ እና ጠቅላላ ጉባኤ በስኬት ለማስተናገድ ዝግጁ እና ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል
በሰብአዊ መብቶች ተኮር አሠራር፣ በሽግግር ፍትሕ፣ በአረጋውያን መብቶች እና በተጠርጣሪዎች መብቶች ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች ለተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሰጥተዋል
በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት ችግሩን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ እና ልዩነቶችን በሕግ መሠረት በምክክርና በመግባባት ለመፍታት እንዲሠሩ ኢሰመኮ ያሳስባል
ኢሰመኮ ከፌዴራል እና ከክልል መንግሥታት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ያደረጋቸው ተከታታይ ውይይቶች የሰብአዊ መብቶች ጥበቃን በማጠናከር እና ጥሰቶችን በመከላከል ረገድ አበረታች ውጤቶችን አስገኝተዋል