የምክትል ዋና ኮሚሽነር እና የሰብአዊ መብቶች ዘርፎች ኮሚሽነሮች መሾም፣ የአመራር ቀጣይነትን እና የተሳለጠ የሥራ ሽግግርን ከማረጋገጡም በላይ ኮሚሽኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት ያለውን ዐቅም ይበልጥ ያጠናክረዋል
ኢሰመኮ ገለልተኛ ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ መብቶችን ለማስከበር ያላቸውን ወሳኝ ሚና በመገንዘብ፣ የዶ/ር አብዲ ጅብሪል ዓሊን ለ CESCR መመረጥ ያደንቃል
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው፣ የተጎጂዎችን ሰብአዊ መብቶች ያከበረ፣ የተቀናጀ እና አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ አሳስበዋል
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በሰዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እና መፈናቀል እልባት ለመስጠት የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል መንግሥታት በዞኑ በቂ የጸጥታ አካላትን ማሰማራትና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ጨምሮ አፋጣኝ፣ ተጨባጭና ዘላቂ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል
በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት ችግሩን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ እና ልዩነቶችን በሕግ መሠረት በምክክርና በመግባባት ለመፍታት እንዲሠሩ ኢሰመኮ ያሳስባል